Heading

HOMEAbout UsMunicipal OrgansProjectsNEWSContact UsFeedback

መመመመመመመመመመመመ

Municipal News

መመመመመመመመመመመ

 

በሀረር ማዘጋጃ ULGDP ማስተባበሪያ ጽ/ቤት እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች

Posted on Tuesday, June 30, 2009

በሀረር ማዘጋጃ ULGDP ማስተባበሪያ ፅ/ቤት እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ጠቅላላ ገፅታ 

  1. የሀረር ማዘጋጃ ULGDP ማስተባበሪያ ፅ/ቤት በአለም ቅርስነት የተመዘገበውን ጀጎል ግንብ ዙሪያ መንገድ በምርጥ ጌጠኛ ድንጋይ (cobblestone) ግንቦት 12/09/2001 ማሰራት የተጀመረ፡፡

  2. በሶስት የቀበሌ መስተዳድሮች ለሚሰራው የጎርፍ መከላከያ ግንብ ጨረታ በ February 7/09 ቀን ታውጆ የጨረታው አሸናፊ ከታወቀ በሀላ ሥራው በአስቸካይ እንዲጀመር የሳይት ርክክብ ተፈፅሞ በሶስቱም ቀበሌ መስተዳርሮች ውስጥ ስራው እየተከናወነ ይገኛል፡፡

  3. ሶስት መቶ ሀምሳ በኮብል ስቶን ዝግጅት ስልጠና የወሰዱ ወጣቶች በ19 መሀበራት የተደራጁ ሲሆን በጥሩ ሁኔታ በማምረት ስራ ላይ የተሰማሩ ከመሆናቸውም ባሻገር ባመረቱት መጠን ልክ ክፍያቸውን እየተረከቡ ይገኛሉ ፡፡

  4. የሀረር ማዘጋጃ ULGDP ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ከሀረር ተቪቲ ኮሌጅ ጋር ጥምረት በመፍጠር ያሰለጠናቸውን 320 ኮብል ስቶን አምራች ወጣት ማህበራት ግንቦት 15/09/2001 በሰርተፊኬት አስመረቀ፡፡ ለነዚሁም ወጣቶች በረጅም ግዜ ክፍያ ብድር ውል በማስገባት ዋጋው ብር 197000.00 ብር የሆነ ምርጥጌጠኛ ድንግይ ማምረቻ እቃዎች በመግዛት ለየመሀበራቱ አከፋፈለ (cobblestone) የማምረቻ እቃዎች አከፋፈለ፡፡

  5. በ May 28/09 ቀን በታተመው ሄራልድ ጋዜጣ በሀረር ከተማ እንዲሰሩ ለታቀዱት ሁለት ደረጃቸውን የጠበቁ ቄራዎች እና  የከተማ ውበት  ማበልፀግ ግንባታ   (urban greenery ) ግንባታ የጨረታ ማስታወቂያ አወጣ፡፡

  6. በ June 29/09 በሀረር ማዘጋጃ ULGDP ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የቄራ ግንባታ ጨረታ ተጫራቾች በተገኙበት ተከፈተ፡፡

View Photo Gallery

የከተሞች መሠረት ልማት ማስፋፊያ ፕሮጀክት (ULGDP)

Posted on Saturday, March 21, 2009

የሐረር ማዘጋጃ ቤት የአዲሱ የከተማ መሠረተ-ልማት ማስፋፊያ ፕሮጀክት የ (ULGDP) ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በ6 የቀበሌ መስተዳድሮች (በአባድር ቀበሌ መስተዳድር፣ አሚር ኑር ቀበሌ መስተዳድር፣ በጄኔኤላ ቀበሌ መስተዳድር፣ በሸንኮር ቀበሌ መስተዳድር፣ በሐኪም ቀበሌ መስተዳድር፣ እና በአቦከር ቀበሌ መስተዳድር የሚኖሩ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን የሲቪክ ማህበራትን ወዘተ… የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በማዘጋጀት ሠፊ ገለፃ ካካሄደ በኋላ ህብረተሰቡ ቅድሚያ የሚሠጣቸው የልማት ሥራዎችን በመለየት ከህብረተሰቡ ጋር በቀጣይነት የሚሠሩ የልማት ሥራዎች ላይ ዕቅድ ነድፏል፡፡

      የሐረር ማዘጋጃ የአዲሱ የከተማ መሠረተ-ልማት ማስፋፊያ ፕሮጀክት (ULGDP) ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በየካቲት 30/2001 ዓ.ም ለ 17 የኮብል እስቶን አምራች ማህበራ በኮንትራት ውል በተፈራረሙበት መሠረት የ 10% የቅድመ ክፍያ ብር 413,445 ( አራት መቶ አስራ ሶስት ሺህ አራት መቶ አርባ አምስት ብር) ከፍሏል፡፡

     የሐረር ማዘጋጃ ቤትን የሒሳብ አያያዝ ስርዓት ግልፅነትና ተጠያቂነት ሊያሰፍን እና ሊያረጋግጥ የሚችል የአሠራር ሥርዓት ለማዳበር ወደ 20 ለሚሆኑ የሒሳብ ባለሞያዎችና የውስጥ ኦዲተሮች በሁለት ዙር ለ24 ቀናቶች የከተማው መስተዳደር ከ GTZ አማካሪዎች ጋር ጥምረት በመፍጠር በኦዲት፣ በሒሳብ አያያዝና ሥርዓት፣ እና በበጀት ዝግጅት አፈፃፀም ላይ በተግባር እና በቲዮሪ ላይ የተመሠረተ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

      የሐረር ማዘጋጃ የአዲሱ የከተማ መሠረተ-ልማት ማስፋፊያ ፕሮጀክት (ULGDP) ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በጀጎል ዙሪያ ያለውን መንገድ በኮብል ስቶን (በምርጥ ጌጠኛ ድንጋይ) ለመስራት ባቀደው መሠረት በግሬደር የጠረጋ ሥራ እያከናወነ ነው፡፡

      የሐረር ማዘጋጃ የአዲሱ የከተማ መሠረተ-ልማት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት (ULGDP) በመጋቢት 1/2001 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 የጎርፍ መከላከያ ኮንስትራክሽን ጨረታ ተወዳዳሪዎችና ተጫራቾቹ በተገኙበት ተከፈተ፡፡

አዲሱ የኢትዮጵያ የከተሞች መሠረት ልማት ማስፋፊያ ፕሮጀክት (ULGDP) በሀረሪ ብ/ክ/መንግስት ያለው ገፅታ

Posted on Wednesday, February 2, 2009

በመጀመሪያ ደረጃ ይህ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ መንግስትና በዓለም ባንክ እየተከናወኑ ያሉ የተለያዩ ፕሮግራሞች መሐከል በአቅም ግንባታ ላይ ያተኮረ እና በአተገባበሩ ልዩ  የሆነ ሲሆን 19 ከተሞችን ያቀፈ ፕሮጀክት ነው፡፡ ይህም በግልፅ የተበሠረው በአዲስ አበባ ከ November 21 - 22/2009 በጊዮን ሆቴል በተካሄደው ወረክ ሾፕ ላይ ነው፡፡

የሐረር ከተማ የአዲሱ የከተማ መሠረት-ልማት ማስፋፊያ ፕሮጀክት (ULGDP) በቀጣይ 3(ሶስት) አመታት በድምሩ ብር 65.9 ሚሊዩን በጀት የተመድበለት ሲሆን ከዚህ ውስጥ

  • የአለም ባንክ ብድር 47 ሚሊዩን ብር

  • የክልሉ መንግስት መዋጮ 9.3 ሚሊዩን ብር

  • የማዘጋጃው መዋጮ 9.3 ሚሊዩን ብር

በቀጣይ 3 (ሶስት) አመታት የሚተገብራቸው ንዑሳን ፕሮጀክቶች በሚከተሉት ዘርፎች ላይ ያጠነጥናሉ

  • በመንገዶች ግንባታ

  • የጎርፍ መከላኪያና ማስወገጃ

  • የቆሻሻ ውሃ ማስወገጃና ማጠራቀሚያ ግንባታ

  • የጆጎል ቅርስ ጥበቃ ሥራዎች

  • የቄራ ግንባታ

  • የመናኸሪያ ግንባታ

  • የገበያ ቦታዎች ግንባታ

  • አረንጓዴ አከባቢዎች(መናፍሻዎች) ዝግጅት

  • ለተለያዩ የልማት ተግባራት የሚውል የመሬት ዝግጅት

  • የመንገድ ላይ መብራት እና የመሳሰሉት ይገኝበታል፡፡

በዚሁ መሠረት በዘንድሮ 2001 በጀት አመት 6 ንዑሳን-ፕሮጀክቶች በአለም ባንክ በኩል ተቀባይነት ያገኙ ሲሆን እንዚህም

  1. ሁለት የገበያ ቦታዎች

  2. የጀጎል ዙሪያ መንገድ በምርጥ ጌጠኛ ድንጋይ /Cobble stone/ይሠራል

  3. በተለያዩ የሐረር ከተማ አካባቢዎች የጎርፍ መከላከያ ግንብ ይሠራል

  4. የተለያዩ የልማት ሥራዎች የሚውል የመሬት ልማት ዝግጅት

  5. የጆጎል ቆሻሻ ውሃ ማጠራቀሚያ/Septic thank/ይሠራል

  6. ሁለት ደረጃቸውን የጠበቁ የቄራ ሥፍራዎችን ይሠራል፡፡

ከላይ የተጠቀሱትን ፕሮጀክቶችንና በቀጣይ 2 አመታት የሚተገበሩ ንዑሳን ፕሮጀክቶችን ውጤታማ ለማድረግ በሐረር ከተማ ማዘጋጃ የ(ULGDP) ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከጥር 1/2001 ጀምሮ ዓ.ም ተቋቁሞ ሥራ የጀመረ ሲሆን የጽ/ቤቱም አድራሻ በሐረር ከተማ ማዘጋጃ ግቢ ውስጥ ነው ጽ/ቤቱን በሠው ኃይል ለማደራጀት ከሐረር ማዘጋጃ እና ከክልሉ ሥራ እና የከተማ ልማት ቢሮ በተለያዩ ሞያ የተመረቁና ብቁ ባለሞያዎች ባጠቃላይ 13 ማለትም 8 በቋሚነት 5 በተደራቢነት የሚሠሩ ሠራተኞችን በኮንትራት ከመቅጠሩም በሻገር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሥራዎች ማከናውኑን በመጥቀስ ጽ/ቤቱ በይፋ ሥራ መጀመሩን ለመረዳት ያስችላል፡፡

ወቅታዊ ሁኔታ( Status ) በተመለከተ

  1. የቀላድ አንባ  የገበያ ቦታ ግንባታ የጨረታ ማስታወቂያ Ethiopian Herald Feb 7/2009 የወጣ ሲሆን የጨረታ ሰነዱም እየተሸጠ ይገኛል

  2. የ3 ቦታዎች የጎርፍ መከላከያ ግንባታ ሥራ የጨረታ ማስታወቂያ Ethiopian Herald Feb 7/2009 የወጣ ሲሆን ሰነዱም በመሽጥ ላይ የገኛል

  3. የጆጉል ዙሪያ የኮብል ስቶን ኮንስትራክሽን በተመለከተ ፕሮጀክት ማስተባበሪያው በሐረሪ ክልል ከሚገኙ 19 ኮብል ስቶን ኮንስትራክሽን ማህበራት ጋር ብር 5 ሚሊዩን የሚያወጣ ኮንትራት የተፈራረመ ሲሆን የሥራውም መጠን 7159 m2 አካባቢ ይሆናል፡፡

  4. የቄራ እና የጆጉል ቆሻሻ ውሃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ ግንባታ በዘንድሮ በጅት አመት በተፈጠረው የጊዜ እጥረት የኮንስልታንሲ ተግባራትን ብቻ ዘንድሮ በማከናወን የግንባታውን ሥራ በቀጣይ 2002 በጀት አመት ለማከናወን የድረጊት መረሀ-ግብር ተዘጋጀቷል

በተጨማሪም ሐረር ከተማ የ(ULGDP) ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የመጀመሪያውን የግንዛቤ ማስጨበጫ አውደ-ጥናት ቅዳሜ ጥር 30/2001 በአሚር አብዱላሂ አዳራሽ አካሂዷል፡፡ በአውደጥናቱም ላይ የአከባቢ ቀበሌዎች አስተዳድር የምክር ቤት አባላት እና በተለይ በዚህ ዓመት የሚሠሩ የልማት ተግባራት ቀጥተኛ ተጠቃሚ የሆኑ የህብረተስብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡

መድረኩን የመክፈቻ ንግግር አድርገው የከፈቱት የሐረር ከተማ ሥራ አስኪያጅ አቶ ተወለዳ አብዶሽ ሲሆኑ በመቀጠልም የሐረር ከተማ (ULGDP) ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አባላት እና የጽ/ቤቱ ምክትል ኮኦርዲነትር አስፈላጊ የሆነ የግንዛቤ ማስጨበጫ ማብራሪያ ሠጥተዋል፡፡

በመጨረሻም መድረኩ ለአውደ ጥናቱ ተካፋዮች ክፍት በመደረጉ ተሳታፊዎች በፁሑፍ በጥያቄ እና መልስ ንቁ ተሳትፎአቸውን አሳይተው አስፈላጊውን የህብረተሰብ ተሳትፎ የ(ULGDP) ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በጠየቃቸው ጊዜ ለማድረግ እና ለመሳተፍ ቃል ገብተዋል፡፡

በሀረር ከተማ የ‘GIS’ ስራ ለመጀመር ስምምነት ተፈረመ

Posted on Wednesday, August 21, 2008

በሀረር ከተማ ያለውን የመሬትና ተዛማች መረጃዎች በዘመናዊ መልኩ ለማደራጀት ፣ ለመምራትና ለመቆጣጠር እንዲያስችል በ10 (አስር) ሚሊዮን ብር የ ‘Geographic Information System’ ስራ ለመጀመር የውል ስምምነት በኢትዮ ጃፓን (EJI) ኩባንያና በሀረር ከተማ መካከል የስራ ውል ስምምነት ነሀሴ 13/2000 ዓ.ም ተፈረመ፡፡                                      

ስምምነቱን የሀረር ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዐሪፍ መሐመድና የEJI ኩባንያ ተወካይ አቶ ኻሊድ ዩሱፍ ፈርመዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በዚህ ዓመት የሚጀመር ሲሆን በከተማዋ ያለውን ዝርዝር የመሬት ፣ የቤት ፣ እንዲሁም የሌሎች መሠረተ ልማቶች ዘመናዊ በሆነ መልኩ በሳተላይት አማካኝነት በማደራጀት የአገልግሎት አሰጣጥ ችግርን በዋናነት እንደሚቀርፍና የከተማዋን ገቢ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳድግ ተገልጿል፡፡

View Photo Gallery

የሀረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት ለ2001 በጀት ዓመት 65 ሚሊዮን ብር በጀት መደበ

Posted on Wednesday, August 21, 2008

የሀረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት የ2000 በጀት ዓመት እቅድ ክንውኑን ለከተማው ህዝብ ነሀሴ 3/2000 ዓ.ም ያቀረበ ሲሆን በዚህም ባለፈው በጀት ዓመት የከተማው ማዘጋጃ ቤት ያከናወነው የልማት እንቅስቃሴ አበረታች እንደነበረና በዚሁ ህብረተሰቡን በማሳተፍ ማዘጋጃ ቤቱ የልማት እንቅስቃሴውን መቀጠል እንደሚገባው ተጠቆመ፡፡

የክልሉ ፕረዝደንት ክቡር አቶ ሙራድ ዐብዱልሃዲ በውይይቱ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር የክልሉ መንግስት የማዘጋጃ ቤቱን እንቅስቃሴ ለማጠናከር ስር ነቀል ለውጥ እያደረገና ለከተማው ልማት ልዩ ትኩረት እየሰጠ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የከተማው ሥራ አስኪያጅ አቶ ዐሪፍ መሐመድ ዝርዝር ሪፖርቱን ለህዝብ ያቀረቡ ሲሆን በቀጣይ ዓመትም በመንገድ ግንባታና ጥገና ፣ በኤሌክትሪክ በገበያ ቦታዎች ግንባታ ፣ በከተማ ጽዳትና ውበት ስራዎች አጠናክረው እንደሚቀጥሉና ለ2001 በጀት ዓመትም ለከተማው ከምንም ጊዜውም የበለጠ በጀት ብር 65 ሚሊዮን በመመደብ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን ገልፀው ፤ የውይይቱ ተሳታፊዎች በዝርዝር ከተወያዩ በኋላ ህዝቡ በቀጣይ በከተማው ማዘጋጃ ቤት ጎን በመሆን አስፈላጊውን ተሳትፎ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡

Harar and Charleville Sister Cities Relation

Posted on Sunday, Jun 29,2008

The delegations of Charleville-Mézières city pay a four day working visit to Harar. Mayor Claudin Leadux and her delegations held deep discussion with Harari region officials.

 Since May 2005 (sister cities relation signed in France), the two cities have cooperated on social, economic and cultural activities, such as water and sanitation, women training and urban development planning.

Mayor Claudin has promised to provide further assistance to the city of Harar, such as provision of surgical equipment, fire hazard safety equipment and other assistants on request for the coming year.

In order to strength the relation and cooperation of the two cities, the road from Harar Ras Hotel to Benat Supermarket, is named “Charleville Street".

View Photo Gallery

German Delegation Visit Harar

Posted on Sunday, Jun 08, 2008

A delegation led by German parliament member Dr. Stasch attend a one day visit to Harar. The delegation met with the regional cabinet members in order to evaluate the GTZ (German Technical Cooperation) urban projects and to strengthen further assistance to the city of Harar in local development planning. During the meeting, Harar city manager Arif Mohammed briefed the delegation, on the current developmental activities of the municipality of Harar on local developmental projects.

የማንዚኒ (Swaziland) እና የሀረር ከተማ ትብብር

Posted on Sunday, Jun 01, 2008

በደቡብ አፍሪካ አገሮች አከባቢ የምትገኝ እና የስዋዚላንድ ሁለተኛ ከተማ በሆነችው ማንዚኒ እና በሀረር ከተማ መካከል ወደፊት ስለሚኖር የባህል፣ የማህበራዊ እና የኢኮኖሚ የጋራ ትብብር የሁለቱ ከተሞች አመራሮች በመግባቢያ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡ ለሁለት ሳምንት የስራ ጉብኝት ለማድረግ የሀረር ከተማ ስራ አስኪያጅ አቶ ዐሪፍ መሐመድ እና የንግድ ኢንዱስትሪ እና ከተማ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ኢሊያስ ዐብዱማሊክ ከማንዚኒ ከተማ ከንቲባ እና ከከተማው ባለስልጣናት ጋር ሰፋ ያለ ውይይት አድርገዋል፡፡ በዚሁ መሰረት በቀጣይ የሁለቱ ከተሞች አመራሮች በከተማዎቹ ስለሚደረጉ የትብብር ግንኙነቶች በጋራ እንደሚመካከሩ እና የእህትማማችነት ስምምነት እንደሚያደርጉ ታውቋል፡፡

Click here to see pictures

Harar Municipality Lend Br.1million to Sheikh Abubakar School

Posted on Wednesday, May 07, 2008

It is noticed that Sheikh Abubakar School has started constructing a three storey market building in order to generate an income to the school. The construction work (the project) has been undertaken by a long term loan fund from the World Islamic Development Bank. According to the Waqf committee head, Abdullahi Wabar, the construction of the project has stopped since last year mainly due to lack of fund. In this regard the Harar municipality has given a due attention to the project and lend one million birr to the school in order to accomplish the project.

በሐረር ከተማ የመሬት የሊዝ እዳ አከፋፈል ውዝግብ አስነሳ

Posted on Thursday, May 01, 2008

በሐረር ከተማ የተሰማሩ ኢንቨስተሮች ከአስር አመት በላይ የተጠራቀመ የመሬት የሊዝ እዳ ክፍያ እንድንከፈል ተጠይቀናል ሲሉ አማረሩ፡፡ የከተማው መስተዳድር የክፍያው ሁኔታ ፍትሐዊ መሆኑን በመግለፅ አቤቱታውን አስተባበለ፡፡

 

በሐረር ከተማ በኢንቨስትመንት መስክ የተሰማሩ ባለሀብቶች፤ ከ1986 ዓ.ም. ጀምሮ ታሳቢ የሚደረግ የሊዝ እዳ ክፍያ መጠየቃቸውን በመግለፅ፤ የእዳ እሳቤውን ተቃወሙ፡፡ ባለሀብቶቹ አንደኛ ደረጃ በካሬ ሜትር 650 ብር ሁለተኛ ደረጃ 550 ብር፣ ሦስተኛ ደረጃ 5ዐዐ ብር ታሳቢ የሚደረግ ክፍያ መጠየቃቸውን አስታውቀዋል፡፡ በዚህም የመሬት ርክክብ ሲደረግ የክፍያ መጠኑ ያልተወሰነ መሆኑን በመጥቀስ ፍትሐዊ ያልሆነ ከፍተኛ ክፍያ መጠየቃቸውን ገልፀዋል፡፡


ባለሀብቶቹ ከከተማው አስተዳደር ጋር የኢንቨስትመንት ውል ሲገቡ የክፍያ መጠን ካሬ ሜትር ተተምኖ ያልተገለፀላቸው መሆኑን በመጥቀስ፤ አስተዳደሩ ያስታወቃቸው የሊዝ ክፍያ መጠን ድንገተኛ እንደሆነባቸው ገልፀዋል፡፡ በዚህም "የከተማው አስተዳደር ከውል ውጪ ከፍተኛ ክፍያ ጠይቆናል" ሲሉ አማርረዋል፡፡

ባለሀብቶቹ የከተማው አስተዳደር የክፍያ ሁኔታውን ለረዥም ጊዜ ሳያሳውቃቸው ቆይቶ፤ በያዝነው ወር ድንገተኛ የክፍያ ውዝፍ መግለፁን ተቃውመዋል፡፡ በተሰጣቸው መሬት ላይ ግንባታ ማከናወናቸውን በመጥቀስ፤ በቅርቡ የተገለፀላቸውን የሊዝ እዳ ለማስከፈል አስተዳደሩ በመሬቱ ላይ የገነቡትን ግንባታ በመያዣነት እንደያዘባቸው ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም የከተማው አስተዳደር ከአስር ዓመት በላይ የተጠራቀመውን እዳ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲከፍሉ ማስገደዱን ጠቅሰዋል፡፡ እንደ ባለሀብቶቹ ገለፅ አንድ ባለሀብት በሊዙ እሳቤው ከአንድ እስከ አራት ሚሊዮን ብር ለመክፈል የሚገደድ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ባለሀብቶቹ የሊዝ ክፍያውን በመቃወም የፊርማ ማሰባሰብ ሥራ መጀመራቸውን ገልፀዋል፡፡ የተቃውሞ ፊርማውንም ለሚመለከታቸው የከተማው፣ የክልሉና የፌደራል መንግሥት አመራሮች እንደሚያስታውቁ ገልፀዋል፡፡

የሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ አሪፍ መሀመድ በበኩላቸው የክልሉ ምክር ቤት እስከ 1999 ዓ.ም. ድረስ የሊዝ ደንብ ያልነበረው መሆኑን ጠቅሰው፤ "የሊዝ ደንቡ ትግበራ መዘግየቱ የክልሉ አስተዳደር ችግር ነበር" ሲሉ ገልፀዋል፡፡ አቶ አሪፍ የሊዝ ደንቡ ዘግይቶ ቢፀድቅም ኢንቨስተሮች እዳቸውን መክፈል እንደሚገባቸው ገልፀዋል፡፡

የክፍያው ሁኔታ በተለያየ የከተማው የይዞታ ደረጃ በካሬ ሜትር ከ150 እስከ 650 ብር መሆኑን የገለፁት አቶ አሪፍ፣ ባለሀብቶች የሊዝ አዋጅ በፌዴራል ደረጃ ከወጣበት ከ1986 ዓ.ም. ጀምሮ ያለባቸውን እዳ መክፈል እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡ የአከፋፈሉ ሁኔታ ግን በአንድ ጊዜ አለመሆኑን ሥራ አስኪያጁ ገልፀው፤ የክፍያ ጊዜውን በተመለከተ መመሪያ የማውጣት ሥራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አቶ አሪፍ በከተማው በኢንቨስትመንት የተሰማሩ ባለሀብቶች መሬት ሲረከቡ በሊዝ ደንብ ክፍያ ለመፈፀም በገቡት ውል መሠረት ክፍያ እንዲፈፅሙ መደረጉ አግባብ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ "ባለሀብቶቹ አሁን የተጠየቁት ውዝፍ እዳ እንዲከፍሉ ሳይሆን፤ የ2ዐ በመቶ የቅድሚያ ክፍያ ነው" ሲሉ አስተባብለዋል፡፡ የከተማው ባለሀብቶች በሊዝ ህጉ መሠረት የሊዝ ውለታቸውን እንዲፈርሙ፣ አዲሱን የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እንዲወስዱ ስራ አስኪያጁ አሳስበዋል፡፡

ሥራ አስኪያጁ የከተማው አስተዳደር ባለሀብቶቹ የሀያ በመቶው የቅድሚያ ክፍያ ውጭ ያለውን የውዝፍ ሂሳብ አከፋፈል በተመለከተ ፍትሀዊ የክፍያ ጊዜ እያመቻቸ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በዚህም የክፍያ ጊዜው እስከ ሀያ አመት ሊደርስ እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

በቅድሚያ ክፍያ አከፋፈል መሠረት ሁለት መቶ ካሬ ሜትር የያዘ ባለሀብት ከአርባ እስከ ሀምሳ ሺህ ብር ብቻ የሚከፍል መሆኑን ጠቅሰው፤ "ክፍያው የባለሀብቱን የኢንቨስትመንት ሥራ የሚያደናቅፍ አይደለም" ብለዋል፡፡

ከዚህም ባሻገር በሆቴል፣ በቱሪዝምና በህክምና የተሰማሩ ኢንቨስተሮች ከ50 እስከ 60 በመቶ ቅናሽ እንደሚደረግላቸው አቶ አሪፍ ገልፀዋል፡፡

ስራ አስኪያጁ በከተማው ከተሰማሩት ኢንቨስትሮች አብዛኛው ከ1995 ዓ.ም. ወዲህ ውል የገቡ በመሆናቸው ከፍተኛ ውዝፍ እዳ በባለሀብቱ ላይ እንደማይኖር ገልፀዋል፡፡ ከባለሀብቶች ጋር ውይይት መጀመራቸውንና ከሀያ በላይ ኢንቨስተሮች ክፍያ መጀመራቸውን አቶ አሪፍ ገልፀዋል፡፡

በሀረር ከተማ እየተካሄዱ ያሉት የልማት እንቅስቃሴዎች አበረታች መሆናቸው ተገለጸ

Posted on April 16, 2008

በሀረር ከተማ ባለፉት ሁለት ዓመታት እየተካሄዱ ያሉት የልማት አንቅስቃሴዎች አበረታች መሆናቸው ተገለጸ፡፡ ይህ የተገለጸው ሚያዚያ 30/2000 ዓ.ም በሀረሪ ህ/ብ/ክ/መንግስት ርዕሰ መስተዳደር የተመራው የክልሉ ካቢኔ አባላት በከተማው እየተካሄዱ ያሉትን የአከባቢ ልማት እንቅስቃሴዎች በጎበኙበት ወቅት ነበር፡፡ በዚሁ መሰረት በከተማው ማዘጋጃ ቤት እየተሰሩ ያሉትን የጁገል ውስጥ ለውስጥ የመንገድ ንጣፍ ስራዎች (Cobble Stone) እንዲሁም በጁገል ውስጥ እየተዘረጋ ያለውን የፍሳሽ ማስወገጃ መስመርና በከተማው የተጀመረውን የ20 ኪ/ሜትር አዲስ አስፋልት ግንባታ ለከተማው ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳላቸውና ስራዎቹ በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ መመሪያ ተሰጥቷል፡፡ በተጨማሪም የየአከባቢዎቹ ነዋሪዎችም የተጀመሩት የልማት ስራዎች አበረታች መሆናቸውና ለልማቱ መሳካት ከክልሉ መንግስት ጎን እንደሚቆሙ ለካቢኔ አባላቱ አረጋግጠዋል፡፡

View Picture Gallery

Municipal Conference in Harar

Posted on March 03, 2008

Harar municipality conducted a conference on Feb 23,2008 in harar Amir Abdullahi hall.Several hundreds of harar city dwellers have attended the conference,which assessing the past two years performance of the office and evaluated the coming three years action plan of the city,which costs more than 250 million birr.

Harar City Manager, Arif Mohammed ,briefd and presented a detailed report and the up coming plan of action that the  municipality excute with in three years in Harar.The participants up on their part ,have underlined and put thier deep appreciation and concern that the municipality has been achieving the progress twards Harars' development.Finally the conference has vowed to assist and support the the municipalities endevour twards Harars' development.

 

The Defense Army handover land to Harari Region

Jan 29, 2008

It is noticed that harar was a military garrison town during Haileselasse and Derg era .Thus around two million square meters of the city has been occupied by military camps at different directions, that badly hinders the developmental capacity of harar city. After many efforts  been made by the regional government in order to take the land and utilize for different investment opportunities and housing projects since 2000 ,So the federal defense ministry has shown his sincere cooperation to harari regional government to handover some portion of the land occupied  in earlier time to assist the developmental endeavors of the region .

Based on the agreement reached ,on Jan 29,2008 the representative of the federal defense army handover about 270,000 square meters  (27 hectares)  of the land to Harar city manager Arif Mohammed.

 

More than 30 City developmental Projects will be Implemented in Harar by
The coming Four years

 

In order to bring a tremendous change economically and socially in Harar city about 40 different projects that may cost more than 100 million birr will be addressed by the coming 4 years.

The team of experts from Federal Urban Planning Institute on Jan 10th and 11th, 2008, has given a briefing of the project, to the cabinet members and other officials of the region.

H.E President Murad Abdulhad, has forwarded his deep concern that the Integrated Development Planning of the city will highly benefit the economic and social development of Harar and enhance the over all revenue of the city.

Among the Projects:-
Bus terminal development
• City market development
• Heritage development
• waste disposal development
• Micro and small enterprise development
• Municipal finance Improvement
• Land use Planning (master plan development.

and so on...